አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በመግዛት አቅም ተመጣጣኝነት (Purchasing Power Parity – PPP) በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ መሆኗን የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ሪፖርት አመለከተ፡፡
ኢትዮጵያ በዓመታዊ የመግዛት አቅም ተመጣጣኝነት የሚለካ 558 ነጥብ 93 ቢሊየን ዶላር ዓመታዊ ጥቅል ምርት ማስመዝገቧን ያመለከተው ሪፖርቱ፥ በዚህም ኬንያ እና ታንዛኒያን በማስከተል በቀዳሚነት ተቀምጣለች ብሏል፡፡
በቀዳሚነት የተቀመጡት ሦስቱ ሀገራት በድምሩ 1 ነጥብ 35 ትሪሊየን ዶላር ዓመታዊ የመግዛት አቅም ተመጣጣኝነት ጥቅል ዓቅም ያስመዘገቡ ሲሆን፥ ይህም ከ4 እስከ 19ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሀገራት በጠቅላላ ካስመዘገቡት እንደሚበልጥ ተመላክቷል፡፡