ስፓርት

ጆርዳን ሄንደርሰን ከዓለም ዋንጫ ውጪ ሆነ

By Yonas Getnet

July 06, 2026

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) እንግሊዛዊው ተጫዋች ጆርዳን ሄንደርሰን ከ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ውድድር ውጪ ሆኗል፡፡

የብሬንትፎርዱ አማካኝ ትላንት ምሽት እንግሊዝ ሜክሲኮን 3 ለ 2 ባሸነፈችበት ጨዋታ የማስታወቂያ ቦርድ ለመዝለል ሲሞክር ወድቆ መጎዳቱ ተመላክቷል፡፡

በዚህም ተጫዋቹ ቀዶ ጥገና እንደሚያስፈልገው እና እንግሊዝ በቀጣይ ከምታደርጋቸው ከዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች ውጪ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

ከጉዳቱ በኋላ ሄንደርሰን ወደ ሆስፒታል የተወሰደ ሲሆን÷ ወደ ብሔራዊ ቡድኑ ማረፊያ አለመመለሱም ነው የተገለጸው፡፡

የ36 ዓመቱ ተጫዋች በዘንድሮ የዓለም ዋንጫ 6 ደቂቃ ብቻ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ግልጋሎት ሰጥቷል፡፡