ፋና ስብስብ

የአንጋፋዋ ድምፃዊት ራሔል ዮሐንስ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ

By Yonas Getnet

July 06, 2026

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአንጋፋዋ ድምፃዊት ራሔል ዮሐንስ ሥርዓተ ቀብር በዛሬው ዕለት ተፈጽሟል።

በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ በተለይም በዘመን አይሽሬ እና በባሕላዊ ስራዎቿ የምትታወቀው አንጋፋዋ ድምፃዊትና የዜማ ደራሲ ራሔል ዮሐንስ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።

በዚህም የቀድሞ የሙያ አጋሮቿ፣ አድናቂዎቿ፣ ቤተሰቦቿና ወዳጅ ዘመዶቿ በተገኙበት በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ደብረ ምህረት ሰዓሊተ ምህረት ቅድስት ማርያምና ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል ሥርዓተ ቀብሯ ተፈጽሟል።

በኪነ ጥበብ ህይወቷ በርካታ አይረሴ ድንቅ ስራዎችን ለህዝብ በማበርከት ታላቅ ባለውለታ የነበረችው አርቲስቷ፤ የሁለት ወንድና የአራት ሴት ልጆች እናት ነበረች።