ቢዝነስ

አየር መንገዱ ከሐምሌ 3 ቀን ጀምሮ ወደ ሚዛን አማን ከተማ የቅድመ ምረቃ በረራ ያደርጋል

By Yonas Getnet

July 08, 2026

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሐምሌ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሚዛን አማን ከተማ በሳምንት ሶስት የቅድመ ምረቃ በረራ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

የሀገር ውስጥ የበረራ አድማሱን እያሰፋ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡ ወደ ደብረ ማርቆስ ከተማ የቅድመ ምረቃ በረራ መጀመሩ ይታወሳል፡፡