የሀገር ውስጥ ዜና

የሲሼልስ ፕሬዚዳንት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

By Hailemaryam Tegegn

July 09, 2026

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲሼልስ ፕሬዚዳንት ፓትሪክ ሄርሚኔ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ብልጽግና ፓርቲ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በማሸነፋቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በመልዕክታቸው የምርጫው ውጤት የኢትዮጵያ ሕዝብ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) አስተዳደር ላይ ያለውን ጠንካራ እምነት የሚያመላክት ነው ብለዋል፡፡

ሲሼልስ እና ኢትዮጵያ በመከባበርና በትብብር ላይ የተመሰረተ የረዥም ዓመታት ግንኙነት እንዳላቸው አውስተዋል፡፡