አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኒውካስል ዩናይትድ ሻን ስቱርን ከአያክስ አምስተርዳም ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡
ኒውካስል ዩናይትድ ለ18 ዓመቱ ኔዘርላንዳዊ አማካይ 20 ሚሊየን ፓውንድ እና እየታየ የሚጨመር 3 ሚሊየን ፓውንድ ወጪ በማድረግ ተጫዋቹን የግሉ አድርጓል፡፡
ሻን ስቱርን በእንግሊዙ ክለብ ኒውካስል ዩናይትድ ቤት ለአምስት ዓመታት የሚያቆየውን ውል ተፈራርሟል፡፡
ተጫዋቹ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ለአያክስ አምስተርዳም 24 ጨዋታዎችን አድርጎ አንድ ግብ ብቻ አስቆጥሯል፡፡
ኒውካስል ዩናይትድ ቀደም ሲል በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ባዙማን ቱሬን ከሆፈንሄይም ማስፈረሙ አይዘነጋም፡፡
በሌላ በኩል ኒውካስል ዩናይትድ በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት አንቶኒ ጎርደን ለባርሴሎና እንዲሁም ሳንድሮ ቶናሊን ለቶተንሃም ሆትስፐር አሳልፎ መስጠቱ ይታወቃል፡፡
በተጨማሪም ኒውካስል ዩናይትድ ብራዚላዊውን የቡድኑን አምበል ብሩኖ ጎማሬሽን የሚያጣበት ዕድል ሰፊ መሆኑ በስፋት እየተዘገበ ሲሆን ተጫዋቹ ክለቡን መልቀቅ እንደሚፈልግም አሳውቋል፡፡
በዚህም ክለቡ ቡድኑን ለማጠናከር በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎ እያደረገ ይገኛል፡፡
በመልካም ፈቃዱ