አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምስራቅ ቻይና ጂንጂያንግ ከተማ በጫማ ፋብሪካ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡
የእሳት አደጋው በሁይትንግ ፉትዌር ሕንጻ ላይ የተከሰተ ሲሆን ÷ እሳቱ በተነሳበት ወቅት 240 የሚሆኑ ሠራተኞች በሕንጻው ውስጥ እንደነበሩ ተመላክቷል፡፡
የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ ÷ በተከሰተው የእሳት አደጋ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል፡፡
የእሳት አደጋውን በፍጥነት ለመቆጣጠር እና ለአስቸኳይ የነፍስ አድን ሥራ ከ500 በላይ ባለሙያዎች በሥፍራው መሰማራታቸውን አመልክተዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ የአደጋው መንስኤ በፍጥነት እንዲጣራ እና ለጉዳቱ ምክንያት የሆኑ ሰዎች በጥብቅ እንዲጠየቁ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል፡፡
ጂንጂያንግ 20 በመቶ የሚሆነው የዓለም የስፖርት ትጥቅ ጫማ የሚመረትባት ሲሆን ÷ የቻይና “የጫማ ከተማ” በመባል እንደምትጠራም ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በመልካም ፈቃዱ