አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አቶ ቸሩጌታ ገነነ የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾመዋል። አቶ ቸሩጌታ ገነነ ወደ ሌላ የሥራ ሃላፊነት ከተዛወሩት የቀድሞ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው ጋር የሥራ ርክክብ አድርገዋል። ላለፉት ሁለት ዓመታት የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ ሆነው ያገለገሉት አቶ ቸሩጌታ÷ በዛሬው ዕለት የፋና ሚዲያ ኮርፖሬሸን ዋና ሥራ አስፈሚነት ሥራቸውን ጀምረዋል፡፡ ዋና ሥራ አስፈፃሚው ከማኔጅመንት አባላት ጋርም ትውውቅ አድርገዋል።