ቢዝነስ

የፋይናንስ ተደራሽነትን ለማስፋትና የሴቶች አመራርነትን ለማሳደግ እየተሰራ ነው – ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)

By Yonas Getnet

July 11, 2026

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተደራሽነትን ለማስፋትና የሴቶችን የአመራርነትን ውክልና ለማሳደግ እየተሰራ ነው አሉ የብሔራዊ ባንኩ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በአመራርና መሠረታዊ የፋይናንስ ትምህርት የሰለጠኑ 1 ሺህ ወጣት ሴቶችን አስመርቋል፡፡

ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የፋይናንስ ተደራሽነትን ለማስፋትና የሴቶችን አመራርነት ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

የሴቶች የፋይናንስ ተጠቃሚነት በዚህ ዓመት ማሻሻል ማሳየቱን ጠቅሰው÷ የበለጠ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ መሥራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ በተካሄደው የስኮር ካርድ ግምገማ 32 ባንኮች ማለፋቸው ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም በሀገሪቱ ባሉ ባንኮች ውስጥ ያለውን የሴቶች የፋይናንስ አካታችነትን መሻሻል መከታተል የሚያስችል የሴቶች የፋይናንስ አካታችነት ስኮር ካርድ ይፋ ተደርጓል፡፡