ዓለምአቀፋዊ ዜና

‘ባቪ’ የተሰኘው ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ንፋስ 900 ሺህ ሰዎች አፈናቀለ

By Yonas Getnet

July 11, 2026

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በቻይና እና ጃፓን የተከሰተው ‘ባቪ’ የተሰኘ ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ንፋስ የታይዋን እና ጃፓን ደሴቶችን በመምታቱ ከ900 ሺህ በላይ ሰዎች ቤታቸውን ለቀው እየሸሹ ነው ተባለ፡፡

አውሎ ንፋሱ በምስራቅ እስያ አንዳንድ አካባቢዎች ጉዳት ያስከተለ ሲሆን፤ ይህም የጅምላ መፈናቀል እና የመብራት መቆራረጥ አስከትሏል ተብሏል።

ባቪ አውሎ ንፋስ ወደ ሰሜናዊ ታይዋን እና ጃፓን ደሴቶች በማምራት በንብረት ላይ ውድመት ያስከተለ ሲሆን፤ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች መውደም የተነሳ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጦባቸዋል።

በቻይና ደግሞ አደጋውን በመሸሽ ከ900 ሺህ በላይ ሰዎች ቤቶቻቸውን ለቀው ለመውጣት መገደዳቸውን ተገልጿል።

በአደጋው ቢያንስ የ39 ሰዎች ህይወት አልፏል።

ባቪ ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ንፋስ በዚህ ፍጥነቱ ከቀጠለ በምስራቃዊ የዜጂያንግ ግዛት የምትገኘውን ዌንዙ ከተማ ይመታል ተብሎ መሰጋቱን ገልፍ ኒውስ ዘግቧል።

በእመቤት ሲሳይ