ስፓርት

ማንቼስተር ዩናይትድ አንድሬይ ሳንቶስን አስፈረመ

By Melaku Gedif

July 13, 2026

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 6፣2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ ብራዚላዊውን የመሐል ሜዳ ተጫዋች አንድሬይ ሳንቶስን ከቼልሲ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡

ማንቼስተር ዩናይትድ 48 ሚሊየን ፓውንድ እና እየታየ የሚጨመር 2 ሚሊየን ፓውንድ ለዝውውሩ ወጪ ማድረጉ ነው የተገለጸው፡፡

በተጨማሪም የቀድሞ ክለቡ ቼልሲ ከተጫዋቹ የወደፊት ሽያጭ 10 በመቶ እንደሚያገኝ በዝውውር ውሉ ላይ ተመላክቷል፡፡

የ22 ዓመቱ ተጫዋች በማንቼስተር ዩናይትድ ቤት እስከ 2031 የሚያቆየውን ውል ተፈራርሟል፡፡

አንድሬይ ሳንቶስ በፈረንጆቹ 2023 ከሀገሩ ክለብ ቫስኮ ደጋማ የምዕራብ ለንደኑን ክለብ ቼልሲ በ10 ነጥብ 2 ሚሊየን ፓውንድ መቀላቀሉ ይታወሳል፡፡