አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ የዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ አፈፃፀም 75 በመቶ ደርሷል አሉ፡፡
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ ከከንቲባ ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች ጋር በመሆን በኤ አይ ዩኒቨርሲቲ አረንጓዴ ዐሻራቸውን ማኖራቸውን ገልጸዋል፡፡
“ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ በሚገኘው የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በከተማችን 6 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል አቅደን እየሰራን ነው ብለዋል።
እስካሁን ከ4 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ ችግኞች መተከላቸውን ገልጸው በዚህም በከተማዋ ከተያዘው ዕቅድ 75 በመቶ ያህሉን ማሳካት መቻሉን አስታውቀዋል፡፡
ችግኝ መትከል ብቻውን ከምናልመው ግብ ስለማያደርሰን የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ስራ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ነው ያሉት፡፡