የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች

By Yonas Getnet

July 15, 2026

👉 ቀይ ባህርን ያጣንበት አጋጣሚ የእኩይ ታሪካዊ ክስተት አንዱ መገለጫ ነው።

👉 ኢትዮጵያ ለሺ ዘመናት ያስተዳደረችውን በባለቤትነት የያዘችውን ለራሷም ለከባቢውም መጠቀሚያ ያኖረችውን ቀይ ባህር ያልተመረጠና ያልተወያየ መንግሥት በሸፍጥ ኢትዮጵያን የጂኦግራፊ እስረኛ እንዲያደርግ ያደረገበት ዋና ምክንያት በውስጥ ያለ ስንፍና እንጂ የኢትዮጵያን መሻትና ጥቅም ማስቆም የሚችል ኃይል ስለነበረ፣ ስላለ፣ ስለሚኖር አይደለም። ‌‎ ‎👉 ሁልጊዜም ጥቅማችንን አሳልፈን የምንሰጠው ስንገነባ ያልነበሩ ስንሻኮት እና ስንጣላ የሚያግዣብቡ አሞራዎች ስላሉ ነው። ‎ ‎👉 ህዳሴን ስንገነባ እኛ ጋር ያልነበሩ፤ ከተሞቻችን ሲያሸበርቁ እኛ ጋር ያልነበሩ፤ ልማት ስንሰራ እኛ ጋር ያልነበሩ፤ እርስ በእርስ ስንጨቃጨቅ ግን ከየት መጡ ሳይባሉ ጥይት እና ብር ሲያቀብሉ በሚዲያዎች ፕሮፓጋንዳ ሲነዙ ይታያሉ። ‎ ‎👉 የተከበረው የኢትዮጰጵያ ህዝብ አንድ ነገር ልብ እንዲል እፈልጋለሁ ‎ምንም ጉዳይ በውስጥ ቢያከራክረን እና ቢያጨቃጭቀን እንዲህ በውይይት መፍታት ስለምንችል ለሌሎች ሀይሎች ጥቅም የኢትዮጵያን መሻት እና ብሔራዊ ፍላጎት አሳልፈን የምንሰጥ አይደለንም። ‎ ‎👉 በታሪክ ውስጥ እንክርዳድ ሆነን የምንታይ ዜጎች ላለመሆን እያንዳንዳችን ጥረት ማድረግ ይኖርብናል። ‎ ‎👉 በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ለሚያንዣብቡ አሞሮች መልዕክቴ፤ ከብቱን መርጠን የምንገዛ እኛነን የቅርጫውም ባለቤት እኛ ነን የማንፈልገውን ካልሆነ በቀር የትኛውም አሞራ በጉልበት ከየትኛውም መደብ ላይ አንድ ፍሬ ስጋ መውሰድ እንደማይችል ላረጋግጥላቸው እፈልጋለሁ።

‎👉 ስንፈልግ ለማጋራት ዝግጁ ነን፤ ነገር ግን ለሺህ ዓመታት በማይበጠስ ክር የተሳሰረችው ኢትዮጵያ አሁን ባለው ፕሮፓጋንዳ ትዘናጋለች ጥቅሟን አሳልፋ ትሰጣለች ብሎ መገመት ከንቱ ምኞት ነው።

በእመቤት ሲሳይ