አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል በ2018 በጀት ዓመት ከጥራጥሬና ቅባት እህሎች እንዲሁም ከቡና ወጪ ንግድ 726 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል አለ የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ፡፡
የቢሮው የሰብልና የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ዳይሬክተር አቶ ልንገረው ሀበሻ እንዳሉት ÷ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከተለያዩ ምርቶች የተሻለ የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት በትኩረት ተሰርቷል፡፡
በዚህም ከጥራጥሬ እህሎች ማሾ፣ አኩሪ አተርና ቦለቄ እንዲሁም ከቅባት እህሎች ሰሊጥ፣ ኑግ እና ቡናን ጨምሮ ከ5 ነጥብ 4 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለውጭ ገበያ መቅረቡን አንስተዋል።
ምርቶቹ በተገቢ መንገድና በወቅቱ ወደ ኢትዮጵያ ምርት ገበያ መግባታቸውንና ወደ ውጭ ተልከው የውጭ ምንዛሪ ማምጣታቸውን ገልጸዋል።
በበጀት ዓመቱም ከጥራጥሬና ቅባት እህሎች እንዲሁም ከቡና ወጪ ንግድ 726 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን አመልክተዋል፡፡
በከድር መሀመድ