የሀገር ውስጥ ዜና

ከአልፋሽጋ ባሻገር፡ ሴራና ሽርክና

By sosina alemayehu

July 16, 2026

የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶችና የውስጥ ባንዳዎች ሀገራችንን ለማዳከም የጠነሰሱት ሴራ ሁሉ በህዝባችን እና በመንግስታችን ጽናት እየከሸፈባቸው ሲመጣ፣ አሁን ደግሞ አዲስ የመሰባሰቢያና የጥፋት አጀንዳ አድገርው ወደ አልፋሽጋ ዘወር ብለዋል።

ይህ አካሄድ ዝም ብሎ የድንበር ስብስብ ሳይሆን፣ ከጀርባው ግዙፍ ስልታዊ፣ ወታደራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞችን ለማስከበር የታለመ ቀጣናዊ የጂኦፖለቲካ ቁማ ር ነው።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብቷ እንዳትጠቀም፣ በተለይም የአባይን ወንዝ እንዳታለማና የታላቁ ሕዳሴግድብ ግንባታን ከነበረበት ውስብስብ ችግር አውጥታ እንዳትጨርስ ለማድረግ ዓለም አቀፋዊና ቀጣናዊ ኃይሎች ያልፈነቀሉት ድንጋይ፣ ያልተጠቀሙት ስልት አልነበረም።

ሆኖም ግን የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ በአንድነት በመቆማቸውና የማይናወጥ ጽናት በማሳየታቸው የታላቁ ሕዳሴ ግድብን ግንባታ በተሳካ ሁኔታ በማጠናቀቅ የጠላቶቻቸውን የዘመናት ህልም አምክነዋል።

ይህ የቅጥፈት ካርዳቸው ሲቃጠልባቸው ቀጥሎ የተጫወቱት ካርድ የኢትዮጵያን የባሕር በር ፍላጎት ማዳከም ነበር።

የባሕር በር ፍላጎታችንን ከውጭ ጠላቶች ጋር በማበር የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም ለማጨናገፍና ኢትዮጵያን አንቀው ከብልጽግና ጉዞዋ ለማዘግየት ቢሞክሩም፣ ኢትዮጵያውያን የባሕር በር ጉዳይን የአጋጣሚ ሳይሆን የሕልውናቸው መሠረትና የልማት ዋስትና አድርገው በጽኑ ስላመኑ ይህ ሙከራም ሙሉ በሙሉ ሳይሳካ ቀርቷል።

በተጨማሪም በሀገር ውስጥ ዴሞክራሲያዊና በህዝብ ድምጽ የተመረጠና ተቀባይነት ያለው መንግሥት እንዳይኖር፣ ሀገር እንድትበታተንና ሥርዓት አልበኝነት እንዲነግስ ሌት ተቀን የሰሩ ቢሆንም፣ ሕዝባችን ከንጋት እስከ ሌሊት በሰላማዊ መንገድ ተሰልፎ የሚበጀውን መንግሥት በመምረጥ ሉዓላዊ ውሳኔውን ተግባር አሳይቷል። ደጋግማ ኢትዮጵያ አሸነፈች፡፡

ከሁሉ በላይ በውስጥ ችግሮቻችን ተጠቅመው እርስ በርስ ሊያዋጉን እየተጉ ባሉበት በዚህ ታሪካዊ ወቅት፣የዘመናት ቁስሎቻችንን በራሳችን ጠረጴዛ ዙሪያ ለመፍታት ሀገራዊ ምክክር በመጀመራችን የጥፋት ኃይሎችን ክፉኛ አሳፍረናቸዋል።

ታዲያ ይህ ሁሉ የአጀንዳ ኪሳራና የስትራቴጂ ውድቀት የገጠማቸው የኢትዮጵያ ጠላቶች፣ አሁን የጥፋት ፊታቸውንና የመጨረሻውን የሴራ ካርዳቸውን ወደ አልፋሽጋ አዙረዋል፡፡

👉 ግን ለምን ?

አልፋሽጋ ምንም እንኳን ለም መሬትና የድንበር ውዝግብ መናኸሪያ ብትሆንም፣ የተሰባሰቡባት የኢትዮጵያ ጠላቶች ፍላጎት ከዚያ በእጅጉ የላቀ ነው።

አልፋሽጋን ማዕከል አድርጎ የሚሽከረከረው ውጥረት ሰፊና ውስብስብ በሆነው በቀይ ባሕር፣ በአፍሪካ ቀንድ እና በአባይ ተፋሰስ ላይ ከሚሰራው ታላቅ የሴራ ንድፍ ጋር የተያያዘ ነው።

አልፋሽጋ በዚህ የጂኦፖለቲካዊ የቁማር ሰሌዳ ላይ ከተቀመጡት ትናንሽ ጠጠሮች አንዷ ሆና ብቅ ብላለች። ከዚህ ስውር መርዝ በስተጀርባ ኢትዮጵያን በሁሉም አቅጣጫ ማዳከም፣ ማዋከብና ትኩረ ቷን መበተን ዋነኛው ግብ ነው።

ቀይ ባሕር የኢትዮጵያውያን የትናንት ታሪክ፣ የዛሬ ቁጭት እና የነገ የብልጽግና በር መሆኑ ጊዜ ቢፈጅ እንጅ የተረጋገጠ እውነት ነው፡

ሆኖም ይህ የማይዋጥላቸው የውጭ ባዳዎች በውስጥ ካሉ ባንዳዎች ጋር እጅና ጓንት በመሆን የኢትዮጵያን ትኩረት ለመበተንና እውነታዋን ለማጠልሸት እንደለመዱት ሰሞኑንም የውሸት ፕሮፓጋንዳና ጩኸታቸውን አፋፍመዋል።

በለቅሷቸው ውስጥ ዓለም አቀፋዊ ትኩረትን ለማግኘት ሲሉ አደገኛ ቀጣናዊ ቀውስ እየጠመቁ ይገኛሉ፤ በዚህ ስሌት ውስጥ አልፋሽጋ ከፊት ተቀምጣለች።

👉 ከአልፋሽጋ በስተጀርባ ያለው ስውር ሴራ እና የኢትዮጵያ የማይናወጥ አቋም

የኢትዮጵያታሪካዊ ጠላቶችና የጥፋት ኃይሎች በአልፋሽጋ ሲሰባሰቡ ከግቦቻቸው መካከል አንደኛው ከለም መሬቶቹ በመነሳትና በአልፋሽጋ ሰበብ የታቀዱ ግጭቶችን በመጫር የኢትዮጵያን ሰሜን ምዕራባዊ ክፍል የማያቋርጥትርምስ፣ አለመረጋጋትና የፀጥታ ስጋት ቀጣና ማድረግ ነው።

ሁለተኛው ደግሞ ሀገራችን በምግብ ራስን ለመቻልና የምግብ ሉዓላዊነትንለማረጋገጥ እያደረገች ያለውን ታላቅ ብሔራዊ ጉዞ ለማደናቀፍ ታልሞ የተወጠነ ነው።ለዚህም ዋነኛ ማዕከላቸው ለም የሆኑትን የድንበርአካባቢዎች ምር ታማነት ማውደም ነው።

እነዚህ የጥፋት ኃይሎች በየጊዜው የሚለቋቸው የውሸት ፕሮፓጋንዳዎች፣ ጩኸቶችና በተለያዩ አካባቢዎች የሚፈጥሯቸው ቀውስ ጠመቃዎች ዝም ብለው የመጡ ሳይሆኑ፣ ዓለም አቀፋዊ ጣልቃ ገብነትን ወደ ቀጣናው ለመሳብ የሚደረጉ ጥረቶች አካል ናቸው።

ሆኖም ግን፣ የኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት የዚህን የጂኦፖለቲካዊ ሴራ ጥልቀት ፣ መርዛማነትና ድብቅ ዓላማ በሚገባ ይረዳሉ።

ኢትዮጵያውያን ስለዚህ የድንበሮቻቸው ጉዳይ የሉዓላዊነታቸው፣ የማንነታቸውና የብሔራዊ ክብራቸው መገለጫ እንጂ የውጭ ኃይሎችና የውስጥ ባንዳዎች የጂኦፖለቲካዊ ቁማር ሰሌዳ እንዲሆን ፈጽሞ አይፈቅዱም።

ታሪካዊ ጠላቶቻችን ሀገሪቱ በራሷ አቅም እንድትቆም የሚያስችሏትን ፕሮጀክቶች ለማስተጓጎልና ሕዝብን ለማዋጋት ቢተጉም፣ በእያንዳንዱ ፈተና ውስጥ የሕዝባችን አንድነትና ጥንካሬ ይበልጥ እየተገነባ መጥቷል።

በመሆኑም አልፋሽጋም ሆነች ሌሎች የሀገሪቱ የድንበር አካባቢዎች የሉዓላዊነታችን መከበሪያና የታሪካዊ አንድነታችን ማሳያ ሆነው ይቀጥላሉ እንጂ የጥፋት አጀንዳ ማስፈጸሚያ የመሆናቸው ዘመን አብቅቷል።