አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከጋምቤላ ክልል ጋር በሰው ተኮር ስራዎች ዙሪያ በትብብር እንሰራለን አሉ።
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልዕክት፤ በዛሬው ዕለት ከጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡመድ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
በዚህም በቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤ፣ በኮሪደር ልማት፣ እንዲሁም በሌሎች የሰው ተኮር ስራዎች ዙሪያ እርስ በርስ ልምድ እየተለዋወጥን፣ ትብብራችንን አጠናክረን በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰናል ብለዋል።