የሀገር ውስጥ ዜና

ህገ ወጡ ህወሓት የትግራይን ሕዝብ ከልማት ወደኋላ አስቀርቷል – አቶ ጌታቸው ረዳ

By Mikias Ayele

July 18, 2026

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ህገ ወጡ የህወሓት ቡድን የትግራይን ሕዝብ ከልማት ወደኋላ አስቀርቷል አሉ የዴሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ (ስምረት) ፓርቲ ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ።

ሕገ ወጡ የህወሓት ቡድን በትግራይ ክልል ሕዝብ ላይ እያካሄደ ያለውን አፈና የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ‘አፈሳ ይቁም፤ ሰላም ይስፈን’ በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ተካሂዷል፡፡

በሰልፉ ላይ አቶ ጌታቸው ረዳ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ሕገ ወጡ የህወሓት ቡድን የትግራይ ሕዝብ ጠላት በመሆኑ ዕድሜውን ለማሳጠር መስራት ይገባል ብለዋል።

ቡድኑ ወጣቶችን ወደ ሱዳን በመሸጥ ለጦርነት እየዳረገ መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህንን ድርጊት ለማስቆም መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

የትግራይን ሕዝብ ከልማት ወደ ኋላ ያስቀረውን ቡድን በማስወገድ የትግራይ ክልል ወደ ሰላም እንዲመለስ በጋራ ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ሰልፉ በሕዝብ ስቃይ ላይ የራሱን ኅልውና ለመገንባት በሚፈልገው ህገ ወጥ ቡድን የምንቃወምበትና ለሰላም ያለንን ፍላጎት የምንገልጽበት ነው ብለዋል።

በትግራይ ሕዝብ ላይ ሰላም ሊሰፍን እንደሚገባ ገልጸው፤ የሕዝቡ ህልውና እና ሰላም የሚያሳስበው ሁሉም ወገን አጋርነቱን ማሳየት እንዳለበት ገልጸዋል።