ቢዝነስ

ኢትዮ ቴሌኮም 215 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ገቢ አገኘ

By Hailemaryam Tegegn

July 23, 2026

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም በተጠናቀቀው 2018 በጀት ዓመት 215 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ገቢ አገኘ፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ የተቋሙን የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም አስመልክተው በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም በበጀት ዓመቱ የገቢ ምንጭን በማስፋት በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን አብራርተዋል፡፡

በዓመቱ 215 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ገቢ መገኘቱን ጠቅሰው ÷ በዚህም የእቅዱን 99 ነጥብ 7በመቶ ማሳካት ተችሏል ነው ያሉት፡፡

ከባለፈው ተመሳሳይ ዓመት ጋር ሲነጻጸርም የ33 ነጥብ 2 በመቶ እድገት ማሳየቱን ነው የተናገሩት ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ።

በመላኩ ገድፍ