የሀገር ውስጥ ዜና

ከዓድዋ እስከ ቀይ ባሕር – በህልውናዋ የማትደራደረው ኢትዮጵያ

By abel neway

July 25, 2026

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የራሷን መብት ከማስጠበቅ አልፋ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ያለመገዛትና የአሸናፊነት ማሳያ፣ የነጻነት ተምሳሌት የሆነች ምድረ ቀደምት ሀገር ናት፡፡ ሉዓላዊነቷን በመዳፈር የሚመጡትን አሳፍራ የመመለስ ደማቅ ታሪክ ያላት፡፡በዓድዋ ወራሪ ጠላት ላይ ድል በመጎናጸፍ የራሷን ሉዓላዊነት ከማስከበር አልፋ ለሌሎች በቅኝ ግዛት ስር ለወደቁ ሀገራት የነጻነትና የአሸናፊነት ተምሳሌት መሆኗን ዓለም የመሰከረላት።የዓድዋ ጦርነት መነሻው ኢትዮጵያን በማታለል ለተገዢነት ሊዳርጋት የቋመጠው ፋሺስት ጣሊያን ያሰፈረው ስምምነቷን ያልጠየቀው የውጫሌ ውል አንቀጽ 17 ነበር፡፡ለበርካታ ጊዜ የዓባይ ግድብን ገድባ መጠቀም እንዳትችል የተለያየ አጀንዳ በማንገብ ጦርነቶችን ለማስነሳት ከመስራት ጀምሮ ለማተራመስና ኢትዮጵያን የግጭት ቀጠና ለማድረግ ጠላቶቿ ይሰራሉ፡፡ ግብፅና ሱዳን በዓባይ ጉዳይ ላይ ከ86 በመቶ በላይ ለወንዙ አስተዋጽኦ ያላትን ኢትዮጵያ ያላካተተ ስምምነት አድርገዋል፡፡ኢትዮጵያ ዓባይን ለመገደብ ማሰብ የጀመረችው በቀደሙ ነገስታት ቢሆንም ሁኔታዎችና አጋጣሚዎች በፈቀዱላት ጊዜ ግድቡን አስጀምራ ያለምንም የውጪ እርዳታ በራሷ አቅም በደምና በላብ ማጠናቀቅ ችላለች፡፡የባሕር በሯን እንድታጣ የተደረገውም እንዲሁ ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ የታሪክና የስነ ልቦና ትስስር ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ ባላመነበት እንዲሁም ህዝቡ በወከላቸው አካላት ባልተደረገ ስምምነት፣ ህገወጥ በሆነ መንገድ በጥቅም ትስስር በተደረገ አካሄድ ነው፡፡የኢትዮጵያን ውድቀት የሚሹ ኃይሎች ከህዝብና ሀገር እውቅና ውጪ የሆኑ አጥፊ ስምምነቶችን በማድረግ ሀገሪቷን እስረኛ ለማድረግ ይሞክራሉ፤ ነገር ግን ኢትዮጵያ በውሳኔ ሰጪ አካልነት ያልተካተተችበትን የትኛውንም ስምምነት የመቀበል ግዴታ ውስጥ አትወድቅም። ይልቁን ያለአግባብ ለተካሄደበት ሁሉ የታሪክ ፍትህን ታሰፍናለች፡፡ኢትዮጵያ ለሁሉም ችግር መግባባትን እንደ መጀመሪያ የመፍትሄ ርምጃ ብትወስድም አሻፈረኝ ብሎ ሉዓላዊነቷን ሊዳፈር ለመጣ ግን በአንድ ተሰባስቦ ጠላትን ማንበርከክን አሳምራ ታውቅበታለች፡፡ ጠላቶቿም ይህንን ጠንቅቀው ያውቁታል።ለኔ ብቻ የሚል ሳይሆን የጋራ ጥቅምን መሰረት ያደረገ ዲፕሎማሲዊ አካሄድን የምትከተለው ኢትዮጵያ የኃይል መንገድን ተጠቅመው የሚመጡ፣ ህልውናዋን የሚፃረሩ አካላትንም አሳፍራ የምትመልስበት ብርቱ ክንድ አላት፡፡ከሀገር አልፎ በሌሎች ሀገራት ላይ ለሚካሄዱ የሰላም ማስከበር ዘመቻዎች ቀዳሚ ተሰላፊ በመሆን ለቀጣናው ሳይቀር አይበገሬ የሆነ ስልጡን የመከላከያ ሰራዊት ያላት ሀገር ናት፡፡ኢትዮጵያ የራሷ ያልሆነውን አትጠይቅም፤ ነገር ግን ብሔራዊ ጥቅሟንና ህልውናዋን የሚነኩ ጉዳዮችን ከማንሳትና ሉዓላዊነቷን ከማስከበር ወደ ኋላ አትልም፡፡በቤተልሔም ግርማ