ሐምሌ 8 ቀን የጀመረው የምክክር ጉባዔ ሒደት ተሳታፊዎች ሃሳባቸውን በስፋት እያንጸባረቁ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል፣
መጀመሪያ ላይ ተመካካሪዎቹ 500 አባላት በያዘ ቡድን ተደራጅተው ስለ ሥነ ዘዴዎቹ እንዲያውቁ በማድረግ እንደገና ከ16 ቦታ 50 ሆነው እንዲከፋፈሉ ተደርጓል፣
በመቀጠልም የሃሰብ ሽርሽሩን ለማፍጠን እንደገና አስር አስር ሆነው ተደራጅተዋል፣
እርስ በስር እንዲግባቡ በሚሰራበት ጊዜ በሃሳብ ዙሪያ ጭቅጭቆች ተነስተዋል፤ በምክክር ላይ ከሚጠበቁ ሶስት ዋና ዋና ሒደቶች አንዱ ጭቅጭቅ ነው፣
ለቀጣዮቹ ሳምንታት ወደ ትንንሽ ቁጥር የተከፋፈሉት ቡድኖች ሃሳቦቻቸውን አጠናክረው ለ50ዎቹ ቡድኖች ከዛም ለ500ዎቹ ቡድኖች የሚያቀርቡበት አሰራር ይቀጥላል፣
የምክክር ጉባዔው የመጨረሻ ምዕራፍ የጋራ መግባባት ነው፤ ለዚህም መሳካት አሁን እየተደረጉ ያሉ ውይይቶች ወሳኝ አበርክቶ አላቸው፣
ምክክሩ እስካሁን ባለው ሒደት በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ ነው፣
ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ሰዎች የሃሳብ ልዩነቶቻቸውን አጣጥመው ወደ አንድ የተደራጀ ሃሳብ እስኪያመጧቸው የሚፈጠሩ የሃሳብ ፍጭቶች አሉ፣
በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት የተሳታፊዎችን ባር ኮድ በማመሳከር ትክክለኛው ቁጥር ይገለጻል፣
ተመካካሪዎች በመከባበርና በመደማመጥ በነጻነት ሀሳባቸውን እያንሸራሸሩ ይገኛሉ፣
ለኢትዮጵያ የምክክር ሒደቱ አዋጭና ዘላቂ መፍትሄን ማምጣት የሚያስችል ነው፣
ከ2 ሺህ አጀንዳዎች ወደ 8 የመጡትን አጀንዳዎች የተለያዩ ቡድኖች በተናጥል ወስደው እንዲወያዩባቸው እየተደረገ ነው፣
በእመቤት ሲሳይ