አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በጅማ ዞን በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የለሙ የአቮካዶ ችግኞች ፍሬ መስጠት ጀምረዋል አሉ የዞኑ አስተዳዳሪ ቲጃኒ ናስር።
አስተዳዳሪው እንዳሉት ÷ ባለፉት ዓመታት በ18 ሺህ 316 ሔክታር መሬት ላይ የተለያዩ የአቮካዶ ዝርያዎች መልማታቸውን አስታውሰዋል፡፡
አሁን ላይም ለኢንዱስትሪ ግብዓትነት የሚውሉ የአቮካዶና ሙዝ ምርቶች ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ እየቀረቡ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
በዛሬው ዕለት በዞኑ ሁሉም ወረዳዎች የተመረተ 73 ሺህ ኪሎ ግራም አቮካዶ እና 550 ሺህ ኪሎ ግራም የሙዝ ምርት ለውጭ ገበያ መቅረቡን ገልጸዋል፡፡
የዞኑ አርሶ አደሮች አሁን ላይ ከቢኤምደብሊው ድርጅት ጋር በተፈጠረው የገበያ ትስስር 1 ኪሎ ግራም አቮካዶን በ60 ብር በመሸጥ ተጠቃሚ እየሆኑ ነው ብለዋል፡፡
በዞኑ ከቡና ምርት ቀጥሎ የአቮካዶ፣ ሙዝ እና የማር ምርታማነትን በማሳደግ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡
በወርቅአፈራው ያለው