የሀገር ውስጥ ዜና

በቁልቢ እና ሀዋሳ የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል እየተከበረ ነው

By Yonas Getnet

July 26, 2026

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በየዓመቱ ሐምሌ 19 የሚከበረው የቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል በቁልቢ እና በሀዋሳ ከተማ በታላቅ ሀይማኖታዊ ስርዓት እየተከበረ ይገኛል፡፡

በቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም እየተከበረ በሚገኘው የንግስ በዓል ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ስራ አስኪያጅ ብጹዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብጹዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ እና ሌሎች ብጹአን ጳጳሳት ተገኝተዋል፡፡

በተመሳሳይ በሀዋሳ ከተማ እየተከበረ በሚገኘው የንግስ በዓል ላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሲዳማ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ተገኝተዋል።

ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የመጡ የእምነቱ ተከታዮችና ጎብኚዎች በንግስ በዓሉ ላይ የታደሙ ሲሆን፥ ታቦተ ህጉ ከመንበራቸው ወጥተው በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች በዓሉ በድምቀት እየተከበረ ይገኛሉ።

በመቅደስ ደረጀ እና በጥላሁን ይልማ