የሀገር ውስጥ ዜና

የብሩንዲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ

By amele Demisew

July 26, 2026

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የብሩንዲ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና (ዶ/ር) በ49ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚዎች ም/ቤት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ሹም መላኩ በዳዳ ተቀብለዋቸዋል። ጉባኤው “የአጀንዳ 2063 ግቦችን ለማሳካት ዘላቂ የውሀ አቅርቦትና ደህንነቱ የተጠበቀ የንፅህና አጠባበቅ ስረዓቶችን ማረጋገጥ” በሚል መሪ ሀሳብ ሐምሌ 21 እና 22 በአዲስ አበባ ይካሄዳል በአሸናፊ ሽብሩ