አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል፡፡
ተቋማቱ የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በምስራቅ ሸዋ ዞን ቆቃ የኃይል ማመንጫ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ነው ያከናወኑት፡፡
በዚህም አቮካዶ፣ ፓፓያ እና ሌሎች የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ችግኞችን ተክለዋል፡፡
መሰል ሥራዎች ኢትዮጵያ ለያዘችው በምግብ ራስን የመቻል እና ከተረጂነት የመላቀቅ ውጥን አጋዥ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡
በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምጸሐይ ጳውሎስ እና ሌሎች አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡
በምንተስኖት ሙሉጌታ