አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭትን ለማዘመን የሚያስችል ዲጂታል መተግበሪያ ይፋ አድርጓል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ዲጂታል ስርዓቱ በነዳጅ ዘርፉ የሚታየውን ብልሹ አሰራር ለማስቀረት ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል፡፡
የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ደስታ መኳንንት (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ ተቋሙ የቁጥጥር ስራዎችን በማጠናከርና የነዳጅ አቅርቦትን በማሻሻል ረገድ በርካታ ተግባራት ማከናወኑን አንስተዋል፡፡
በነዳጅ ዘርፍ ሙሉ በሙሉ እንዲሁም በኢነርጂ ዘርፍ በከፊል ዲጂታል አሰራር በመዘርጋት ደንበኞች ባሉበት ሆነው አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ መደረጉ ተመላክቷል።
አሁን ላይ ከ300 በላይ ዝርዝርና 47 ጥቅል አገልግሎቶች በዲጂታል ስርዓት ውስጥ የተካተቱ ሲሆን፥ በቀጣይ ለሕዝቡ ይፋ እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡
በዙፋን አምባቸው