የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከአዘርባጃን ሪፐብሊክ ብሔራዊ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ጋር ተወያዩ

By Mikias Ayele

July 29, 2026

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአዘርባጃን ሪፐብሊክ ብሔራዊ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሳሂባ ጋፋሮቫ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልዕክት፤ ስትራቴጂካዊ አጋርነትን እና የጋራ እድገትን በሚያሳድጉ ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማና ውጤታማ የስልክ ውይይት ማካሄዳቸውን ገልጸዋል፡፡