አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የመንግሥት ተቋማት ላይ ተገልጋዮች ጥያቄ ከሚያነሱባቸው ጉዳዮች መካከል ዋነኛው የአገልግሎት አሰጣጥ አለመዘመን ነው።
ይህም አንድን አገልግሎት ለማግኘት ያለው መባከን የአገልግሎት ፈላጊውን ውድ ጊዜ፣ ገንዘብ እና ጉልበት ያባክናል፡፡
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በአንድ ቦታ የተለያዩ የመንግሥት እና የፌዴራል ተቋማት አገልግሎቶችን ለህዝብ ቀልጣፋና ቀላል በሆነ መልኩ በዲጂታል ሥርዓት እየሰጠ ይገኛል፡፡
አገልግሎቱ ሙሉ ለሙሉ በዲጂታል መንገድ የሚሰጥ በመሆኑ ከብልሹ አሰራር ነጻ እንዲሆን አስችሏል፡፡
ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂ አቀናጅቶ የያዘ ትልቅ ተቋም በመሆን በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ትልቅ ለውጥ በማምጣት መንግሥትና ሕዝብን አቀራርቧል፡፡
የመንግስት ተአማኒነት የሚለካው በሚሰጠው አገልግሎት በመሆኑ የመደመር መንግሥት በቴክኖሎጂ የተደገፈ የአገልግሎት ማዕከል ፈጥሯል፡፡
በዚህም ለመጪው ዘመን የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት ለኢትዮጵያ ብሩህ ተስፋ የሚሰጥ ሆኗል።
ተገልጋዮች መንግሥታዊ አገልግሎት ለማግኘት የሚገጥሟቸውን እንግልት በማስቀረት ጊዜያቸውን እና ገንዘባቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ ዕድል ፈጥሯል፡፡
አገልግሎት ተጠቃሚዎች ወረቀት ተሸክመው ረጅም ሰልፍ የሚሰለፉበትና ከአንድ ተቋም ወደ ሌላ ተቋም የሚንከራተቱበትን ሂደት በማስቀረት ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ አስችሏል፡፡
በትዕግስት ግዛቸው