👉 በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ፍላጎትን በኃይል ለማሳካት፣ ሰዎችን በመግደልና አልጋ ሳይፀና በመገዳደል ስልጣን ለመያዝ የመሞከር አባዜ የባህላችን አንዱ አካል ሆኖ ቆይቷል፡፡ 👉 ይህንንም በልጅ እያሱ፣ በጃንሆይ፣ በደርግ፣ በኢሕአዴግ እንዲሁም በቅርቡ በሰኔ 2010 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ ከተካሄደው ሙከራ ማየት ይቻላል፡፡ 👉 የሰኔ 15ቱ ክስተት ከሌሎቹ የታሪክ አጋጣሚዎች ለየት የሚያደርገው በክልልና በከተማ ደረጃ ዝቅ ብሎ ለመፈጸም የተሞከረ መሆኑ ነው፡፡ 👉 በክልል ደረጃ እንዲህ ያለውን ነገር ፈፅሞ አሳካለሁ ብሎ ማሰብ የስሁት ግምገማ ውጤት ነው፡፡ 👉 በለውጡ ውስጥ ከፍተኛ ሚና ያላቸውን ቢቆዩ ብዙ ሊያበረክቱ የሚችሉ ሰዎችን ያሳጣ ክስተት ነው፤ ይህን የማስታውሰው የታሪካችንና የጠባሳችን አካል አድርጌ ነው 👉 በአንድ መንግሥት ወይም በአንድ ፓርቲ እቅድ የሚመራ ሳይሆን፣ እቅዱን ከተለያየ ምንጭ የሚወስድና እዚህም እዚያም የመሻት ፍላጎቱ የተቀላቀለበት ኃይል በጋራ በሚወያይበት ሒደት ውስጥ ጥፋት ሊያመጣ የሚችል ክስተት ተፈጥሯል፡፡ 👉 አምባቸው መኮንን (ዶ/ር) ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ ለለውጥ ከፍተኛ ጉጉት የነበራቸው፣ ሀሳብና እምነቶችን መቼና እንዴት እናሳካለን በሚለው ላይ ከአማራ ክልል እየመጡ በተደጋጋሚ በመምከርና በመወያየት ከፍተኛ ሚና የተጫወቱ መሪያችን ነበሩ፡፡ 👉ከጀነራል ሰዓረ ጋር ከ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀምሮ የቆየ ትውውቅ ነበረን ፤ በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነትና በለውጡ ዋዜማ በቅርበት ያገለገሉ ታማኝ ሰው ነበሩ፡፡ 👉 በለውጡ ዋዜማ የመጀመሪያ እቅድ ወቅት የጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙንና የደህንነት ኃላፊውን በአንድ ጀምበር ለማንሳት በነበረው ውሳኔ ውስጥ በግንባር ቀደምትነት የተሳተፉና ለለውጡ ሙሉ በሙሉ የታመኑ የሰራዊት መሪ ነበሩ፡፡