አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 26 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በሊባኖስ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር መሾሙን ተከትሎ ሀገሪቱ በፍጥነት አዲስ መንግስት እንድትመሰርት ጠይቀዋል።
አዲሱን የጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ የያዙት በጀርመን የሊባኖስ አምባሳደር የነበሩት ሙስጠፋ አዲብ መሆናቸውም ተነግሯል። ይህንን ተከትሎም ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ሀገሪቱ በፍጥነት አዲስ መንግስት እንድትመሰርት ጠይቀዋል።