የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ኦርዲን በድሪ የክልሉ ሕዝብ በአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ አቀረቡ

By Yonas Getnet

August 02, 2026

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ የክልሉ ሕዝብ በአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ላይ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በነገው ዕለት ለሚካሄደው የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ ባስተላለፉት መልዕክት፥ አረንጓዴ ዐሻራ ከአካባቢ ጥበቃና የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ለሀገራዊ መግባባት፣ ለአብሮነትና ለማህበራዊ መስተጋብር መጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው።

በነገው ዕለት በሚካሄደው የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ ላይ ዐሻራን ማኖር ሀገርን የመውደድ አንዱ የተግባር ማሳያ መሆኑን ገልጸው፥ የክልሉ ሕዝብ በነቂስ በመውጣት ሀገራዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በነገው ዕለት “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ሃሳብ በመላው ኢትዮጵያ የአንድ ጀምበር የችግኝ መርሐ ግብር በማካሄድ 800 ሚሊየን ችግኝ ይተከላል።

በዚህም በሐረሪ ክልል በተመረጡ 14 ቦታዎች ከ300 ሺህ በላይ የደንና የተለያዩ የፍራፍሬ ችግኞች ለመትከል አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቅቋል፡፡