የሀገር ውስጥ ዜና

አረንጓዴ ዐሻራ የበለጸገች ኢትዮጵያን ለቀጣዩ ትውልድ ለማስረከብ ያስችላል – አቶ ጥላሁን ከበደ

By tigist gizachew

August 03, 2026

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ዛሬ ችግኝ የምንተክለው የተሻለችና የበለጸገች ሀገርን ለልጆቻችን ለማስረከብ ነው አሉ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊየን ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በወላይታ ዞን ዳሞት ጋሌ ወረዳ አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል።

‌‎አቶ ጥላሁን በዚህ ወቅት ÷ አሁን ላይ ኢትዮጵያን አረንጓዴ የማልበሱ ተግባር የዜጎች ባህል እየሆነ መምጣቱን አስረድተዋል፡፡

‎ዛሬ የሚተከለው ችግኝ የአየር ንብረት መዘባትን የሚከላከል እንዲሁም የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጥ እንደሆነ አውስተዋል፡፡

የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል ረገድ እያበረከተችው ባለው ሚና በዓለም እንድትታወቅ ማድረጉን አመልክተዋል፡፡

‎በምግብ ራስን የመቻል ጥረትን እውን ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች እየተተከሉ መሆኑን ጠቁመው ÷ ሕብረተሰቡ ችግኝ መትከልን ይበልጥ ባሕል እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

‎በጥላሁን ሁሴን