የሀገር ውስጥ ዜና

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አመራሮችና ሰራተኞች አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኖሩ

By Mikias Ayele

August 03, 2026

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አመራሮችና ሰራተኞች በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል፡፡

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት፥ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ወደ ብልጽግና የምታደርገውን ጉዞ የሚያግዝ ነው፡፡

ኮርፖሬሽኑ ንቅናቄው ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በቋሚነት ችግኞችን ሲተክል መቆየቱን አስታውሰው፥ ይህንን ተግባር አጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት፡፡

ከመትከል ባሻገር ውጤታማ እንዲሆን መንከባከብ እንደሚገባ የገለጹት ዋና ስራ አስፈጻሚው፥ ኮርፖሬሽኑ ይህንን የመከታተል ስራ እየሰራ መሆኑ ተናግረዋል

የኮርፖሬሽኑ አመራሮችና ሰራተኞች በጉለሌ የዕጽዋት ማዕከል ባከናወኑት የችግኝ ተከላ የተለያዩ ፋይዳ ያላቸውን ችግኞች ተክለዋል፡፡

በፌቨን ቢሻው