የሀገር ውስጥ ዜና

ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን የባምባሲ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን መርቀው ከፈቱ

By Hailemaryam Tegegn

August 04, 2026

‎አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ‎የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን የባምባሲ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።

‎የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ በክልሉ ቀደም ሲል ወደ ሥራ ከገቡት የቤጉ-መሶብ እና አሶሳ መሶብ አንድ ማዕከላት በተጨማሪ ሦስተኛው ማዕከል ሆኖ ሥራ ጀምሯል። ‎ ‎በክልሉ አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት በተለያዩ ከተሞች የማስፋት ሥራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመለክታል፡፡