አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክክሩ ለዘላቂ ሰላምና የተሻለች ኢትዮጵያን ለትውልዱ ለማስረከብ ትልቅ ተስፋ የሚጣልበት ነው አሉ ተመካካሪዎች።
በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን የሚወክሉ 4 ሺህ ተመካካሪዎች በስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎች ዙሪያ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ጥልቅና አሳታፊ ምክክር እያካሄዱ መሆኑ ይታወቃል።
በዚህ ምክክር ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ ተመካካሪዎች እንደገለፁት፤ በምክክር ጉባኤው ተሳታፊዎች ሀሳባቸውን በነጻነት የሚያነሱበት ነው፤ ይህም ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር በሚያስችል ሂደት ላይ እንዲቆም አስችሎታል።
ለሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ እንዲሁም የተሻለች ኢትዮጵያን ለትውልዱ ለማስረከብ ትልቅ ተስፋ የሚጣልበት መሆኑንም ተናግረዋል።
የምክክር ጉባኤው ዘላቂ ሰላሟ የተረጋገጠ፣ ለልማትና ለዜጎቿ ምቹ የሆነች ሀገርን ለመገንባት ወሳኝ መድረክ ነው ሲሉ ማንሳታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።