የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያና ቤኒንን ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ያለመው ጉብኝት

By amele Demisew

August 06, 2026

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በቤኒን ሪፐብሊክ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና ፈጠራ ሚኒስትር ማሁና አክፕሎጋን የተመራ ልዑክ የኢፌዴሪ አየር ኃይልን ጎብኝቷል፡፡ የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ ለልዑካን ቡድኑ አቀባበል ያደረጉ ሲሆን ÷ በሀገራቱ የጋራ ጉዳዮች ዙሪያም መክረዋል፡፡ ጉብኝቱ በኢትዮጵያ እና ቤኒን ሪፐብሊክ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ያለመ መሆኑን የመከላከያ ኦንላይን ሚዲያ ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡ መርሐ ግብሩ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ በፈጠራ ሥራዎችና በሕዝባዊ አስተዳደር ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ቁልፍ ተቋማትን በመጎብኘት ሰፊ የልምድ ልውውጥ ማድረግን ያካተተ ነው፡፡ የልዑካን ቡድኑ አባላት በቆይታቸው የአቪዬሽን ከባድ ጥገና ማዕከልን፣ የበረራ ትምህርት ቤትን እና ሌሎች የስልጠና ማዕከላትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡