ስፓርት

ሪያል ማድሪድ ከቪኒሲየስ ጁኒየር ጋር ያለውን ውል እስከ 2032 አራዘመ

By amele Demisew

August 06, 2026

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የስፔኑ ክለብ ሪያል ማድሪድ ከብራዚላዊው የመሥመር አጥቂ ቪኒሲየስ ጁኒየር ጋር ያለውን ውል እስከ ፈረንጆቹ ሰኔ 2032 ድረስ ማራዘሙን ይፋ አድርጓል።

ቪኒሲየስ ጁኒየር በ18 ዓመቱ በፈረንጆቹ ሐምሌ 2018 ሪያል ማድሪድን ከተቀላቀለ በኋላ በክለቡ ባሳለፋቸው ስምንት የውድድር ዘመናት 375 ጨዋታዎችን አድርጎ 128 ግቦችን ሲያስቆጥር፣ 14 ዋንጫዎችንም አንስቷል።

በዚህም 2 የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ፣ 3 የክለቦች ዓለም ዋንጫ፣ 2 የአውሮፓ ሱፐር ካፕ፣ 3 የላሊጋ ክብረ ዋንጫ፣ 1 የኮፓ ዴል ሬይ እና 3 የስፔን ሱፐር ካፕ ይገኙበታል።

ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ወደ እንግሊዙ ክለብ አርሰናል ሊዘዋወር እንደሚችል በርካታ መገናኛ ብዙሃን ሲዘግቡ መቆየታቸው ይታወሳል።