አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አዋሽ 3 የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በጊዜያዊነት አገልግሎት ማቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአዋሽ 2 እና 3 ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ሥራ አስኪያጅ አቶ ዲሳሳ ገልሜሳ በጣቢያው ላይ የጎርፍ መጥለቅለቅ በማጋጠሙ ከቅዳሜ ነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ጣቢያው ለጊዜው አገልግሎት ማቋረጡን አስታውቀዋል፡፡