የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኦቢኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-

By Melaku Gedif

August 08, 2026

👉 የፖለቲካ ነጻነት ወደ ምክክር ያድጋል፤ ምክክር ደግሞ ወደ ህግ የበላይነት ያድጋል፡፡

👉 የህግ የበላይነትን ሙሉ በሙሉ ለማረጋገጥ ህግ ሊቀረጽ፤ ሊወጣ የሚገባው ደግሞ በምክክር ነው፡፡

👉 አሁን ምክክር እየተካሄደ ነው፤ ከዚህ ምክክር የሚወጣው ህግ እኔንም፤ አንተንም፤ ሌላውንም እንዲገዛ ተደርጎ ይወጣል፡፡

👉 አንተ አባት ሆነህ ሌላው አጋር ተብሎ፤ ሁለተኛ ተብሎ ፤ እንደዛ አይሆንም፤ ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች በእኩልነት ዴሞክራሲ መገንባት አለባቸው፡፡

👉 ሀገር ገንብተን፤ ግንድ ሆነን፤ የማዕዘን ድንጋይ ሆነን የመገንጠል ጥያቄ ማንሳትም ትክክል አይደለም፡፡

👉 ኢትዮጵያን ለማፍረስ፤ ኢትዮጵያን ለመበታተን፤ ኢትዮጵያን ለማዳከም የሚፈልጉ ሀይሎች ሀምሳ፤ ስልሳ፤ መቶ ዓመታት በፊትም ነበሩ አሁንም አሉ፡፡

👉 እነዚህ ሀይሎች ትንሽ ሀገር ውስጥ የፖለቲካ ጉዳዮችና መከፋፈል እየተስፋፉ ሲሄዱ ተደርበው ነገሩን ያሰፉታል፡፡

👉 በደም ስልጣን ለመያዝ የመሞከር የፖለቲካ ባህል በዚህ ሀገር ውስጥ እያደገ የመጣ ሲሆን ፤ መቆም ያልቻለና መቆም ያለበት ነው፡፡

👉 የዚህ ሀገር ሰላም የተለይዩ ችግሮች ውስጥ አልፏል፤ በቀጣይ ዓመታት ውስጥ ህዝባችን ግንዛቤ አግኝቷል፤ ሀይላችን ተጠናክሯል፤ ጠላቶቻችን በግልጽ ፍላጎታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ፤ ግንኙነታቸው እየታየ ነው፤ ይህ ይሰበራል፡፡

👉 ዘላቂ፤ ህዝቡን አረጋግቶ የሚያሻግር ሰላም እየመጣ ይሄዳል የሚል እምነት አለኝ፡፡

👉 አሸንፎ መንግሥት ሆኖ ለ27 ዓመታት ሀገርን ከመራ በኋላ ስሙን መቀየር አልቻለም፤ የኢትዮጵያ መንግሥትም ሆኖ ለትግራይ ነጻነት እታገላለሁ ይላል፡፡ ከዚህ ከሄደ በኋላም ይህንኑ ነው የሚያደርገው፡፡

👉 ሕወሓት እኩልነትን መቀበል የማይችል ሃይል ነው፤ ወቅታዊ ሀሳብ፤ ወቅታዊ ሁኔታ፤ የዓለም ሁኔታ ጋር ለመቀየር ዝግጁ አይደለም፡፡

በመልካም ፈቃዱ