👉 የሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ሒደት ሥራዎች በእቅዳችን መሰረት በሚገባ እየተካሄዱ ነው፡፡
👉 እያንዳንዳቸው 500 አባላት ያሏቸው ስምንቱም ቡድኖች ሥራቸውን ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡
👉 በሒደቱ ውስጥ አለመግባባቶች አልነበሩም ማለት አይቻልም፤ እነዚህ አለመግባባቶችና ግጭቶች ምክክሩ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ይበልጥ የተረዳንባቸው ናቸው ፡፡
👉 ተመካካሪዎቹ እነዚህን አለመግባባቶችና ግጭቶች በመደማመጥ መፍታት ችለዋል፡፡
👉 በ500 ተሳታፊ የተቋቋሙት ቡድኖች በቡድን ሲመካከሩ ቆይተው አብዛኞቹ መግባት ላይ የደረሱባቸውን ምክረ ሃሳቦች አጽድቀው አስረክበዋል፡፡
👉 ተመካካሪዎቹ በአብዛኞቹ ጉዳዮች ላይ ተስማምተው ሥራቸውን እያጠናቀቁ ነው፡፡
👉 በምክክር ጉባዔው በስምንቱ ቡድኖች ጸድቀው የሚቀርቡ ምክረ ሀሳቦችን የሚያጣጥም፣ ድግግሞሽ ያለባቸውን ሀሳቦች ወደ አንድ የሚያመጣ ቡድን ዛሬ ስራውን ይጀምራል፡፡
👉 እያንዳንዳቸው 500 አባላት ያሏቸው ስምንቱም ቡድኖች ሥራቸውን ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህም አጠቃለን ለምናቀርባቸው ሀሳቦች ያግዘናል፡፡
👉 ምክክር ጉባዔው ሒደት ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን እየተቀበልን ነው፤ እየመረመርን ውሳኔ እየሰጠን እንሄዳለን፡፡
👉 በአሁኑ ሰዓት 3/4ኛ የሚሆነው ሥራችን እየተጠናቀቀ ነው፤ ቀጣዩ ሥራችን የሚሆነው ለህዝብ ይፋ የማድረግ ሒደት ነው፡፡
በቤተልሔም ግርማ