አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ8 የአጀንዳ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሲመካከሩ የቆዩት የሀገራዊ ምክክሩ አጀንዳ ቡድኖች መግባባት ላይ ደርሰዋል አለ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፡፡
ቀደም ሲል በሰላም ግንባታ፣ በሃይማኖት ጉዳዮች፣ በሙስናና መልካም አስተዳደር እንዲሁም በመንግስት አደረጃጀት እና የፖለቲካ ስርዓት ሲመካከሩ የቆዩት ቡድኖች መግባባት ላይ እንደደረሱ መገለፁ የሚታወስ ነው፡፡
በዛሬው ዕለትም በሀገር ግንባታ፣ በፌዴራል ከተሞች ጉዳይ፣ በተቋማት ግንባታ፣ በሕግ የበላይነትና ሰብዓዊ መብት እንዲሁም በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ቀሪዎቹ አራት ቡድኖች ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡