አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብናልፍ አንዱአለም ከአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሽያ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም በተለያዩ ወቅታዊ ሀገራዊ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ በትኩረት መክረዋል።
በቀጣናው አካባቢ እየተስተዋሉ ያሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት በሚከናወኑ የትብብር መስኮች በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይም ተወያይተዋል።
ወሳኝ የሆነውን የማዕድን ዘርፍ ጨምሮ በሀገራቱ መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር እና ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በሚያስችሉ መንገዶች ላይ በጋራ መስራት እንደሚገባ አጽንኦት መስጠታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።