አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በምክክሩ ኢትዮጵያ ትልቅ ተስፋ ያለት ሀገር መሆኗን አሳይታለች አሉ የአጀንዳ ተመካካሪዎች፡፡
ከተመካካሪዎች መካከል አቶ አሚን ሙሰባ ÷ ከዚህ በፊት በነበሩ መንግስታት የምክክር እድል እንዳልነበር አስታውሰው፣አሁን ላይ ግን ኢትዮጵያውያን ችግሮቻቸውን ለመፍታት ምክክር እያደረጉ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በውይይቱ ወቅት አለመግባባቶች ቢከሰቱም በመመካር ወደ አንድ ሀሳብ እየመጣን እንገኛለን ያሉት አቶ አሚን÷የተስማማንበትን ሀሳብ መንግስት ወደ ተግባር እንዲለውጥልን እንፈልጋለን ብለዋል፡፡
ሌላኛዋ ተመካካከሪ ሀደ ስንቄ አረጋሽ ገዳአባ÷ምክክር ለሀገር ግንባታ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፣ኢትጵያውያን በአንድ ላይ ሲመክሩ ልዩነቶች እንደሚጠቡ እና ይህም ለቀጣይ ትውልድ ሰላማዊ ሀገር ለማስረከብ ወሳኝ መሆኑን አበብራርተዋል፡፡
ጠመንጃ ስልጣን እና ለውጥ እንደማይመጣ በመጠቆም፣ሕዝብ ይህንን በመረዳት ልዩነቶችን በበውይይት ለመፍታት ምክክር እያደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
አቶ በላይነህ ታዘበው በበኩላቸው ÷ በምክክር ጉባኤው ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች መሳተፋቸውን ጠቅሰው፣በምክክሩ ሁሉንም ባግባቡ አጀንዳዎች ላይ ከስምምነት እየተደረሰ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
በምክክሩ ኢትዮጵያ ለወደፊት ትልቅ ተስፋ ያላት ሀገር መሆኗን አሳይታለች ያሉት አቶ በላይነህ፣ምክክሩ ኢትዮጵያውያን ከልዩነት ይልቅ በአንድ አላማ ሀገርን ለማፅናት የሚሰሩበትን እድል ይዞ መጥቷል ብለዋል፡፡
በትዕግስት ግዛቸው