አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሌጅ በሁለተኛ ዙር የሰለጠኑ 864 የፖሊስ መኮንኖች መርቀናል አሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ ተመራቂ የፖሊስ መኮንኖቹ በቆይታቸው ያገኙት እውቀት ለላቀ ፖሊሳዊ ስብዕና የሚያበቃ ነው፡፡
ተመራቂዎቹ ወደ ስራ ሲሰማሩም ያለ አድልዎና ልዩነት በታማኝነት፣ በጀግንነት፣ በሰብዓዊነት እና በክብር ለህግ የበላይነት እንደሚያገለግሉ እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡
በንድፈ ሀሳብና በተግባርና በጠንካራ ስነምግባር ስልጠናቸውን ተከታትለው ላጠናቀቁ የፖሊስ መኮንኖች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡