አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የዜጎቿን የዘመናት ጥያቄዎች ለመመለስ የሚያስችል ታሪካዊ የምክክር መድረክ በማዘጋጀት ለዘላቂ ሰላም የማዕዘን ድንጋይ የማስቀመጥ ሂደት ላይ ትገኛለች።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ከመላው ሀገሪቱ የተወጣጡ ተመካካሪዎችን በማሳተፍ ሀገሪቱን ከተበጣጠሱ የፖለቲካ ውዝግቦች ወደ ተዋቀረና የሰለጠነ የጋራ መግባባት ባህል እያሸጋገራት ይገኛል።
በተናጠል እና በቡድን ውይይቶች ተሳታፊዎች በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ በመምከር ለሀገር አንድነት ይበጃል ያሏቸውን ሀሳቦች በማንሳት እየተወያዩ ይገኛሉ፡፡
በኮሚሽኑ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት የተወካዮች ድምፅ ወደ ተግባራዊ የሀገር ግንባታ ስትራቴጂዎች እቅድ እያደገ ነው።
በመምክክሩ መደምደሚያ በሀገረ መንግሥት ግንባታ፣ በመንግሥት መዋቅር፣ በዘላቂ ሰላም እና የግጭት አፈታት እንዲሁም በህግ፣ በሃይማኖት እና በሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮች የጋራ መግባባት ላይ ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ይህ የምክክር ሂደት የፖለቲካ ልምምድ ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚ እድገት መሰረትም ነው፡፡
የግጭቶችን መንስኤ በመፍታት እና ተቋማዊ ግልጽነትን በመፍጠር፤ ምክክሩ ለሀገራዊ ልማት የጸና መሰረት ይሆናል፡፡
በዋና ዋና አጀንዳዎች ዙሪያ የተደረሰው የጋራ መግባባት ለሀገራዊ የልማት ስትራቴጂዎች ትግበራ መንገድ ይጠርጋል።
በሰፊ ህዝባዊ ስምምነት ላይ በመመስረት የሚጸኑ የፖሊሲ ውሳኔዎች በግብርና ዘመናዊነት፣ በኃይል መስፋፋት፣ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና በስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ያሉ አሁናዊ ጥረቶችን እንሚያጠናክር ይታመናል፡፡
ኢትዮጵያ ከእቅድ ወደ ተግባራዊ አቅጣጫ አፈጻጸም ለምታደርገው ሽግግር ሀገራዊ ምክክሩ የዴሞክራሲያዊ አመራር የዘላቂ ሰላም እና ብልጽግና መመሪያ ሆኖ ያገለግላል።
በምሕረት ደምሴ