ስፓርት

ፖል ፖግባ ከሞናኮ ጋር ተለያየ

By Yonas Getnet

August 19, 2026

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሞናኮ ከፈረንሳዊው ተጫዋች ፖል ፖግባ ጋር መለያየቱን ይፋ አድርጓል፡፡

ፖግባ ከአበረታች ንጥረ ነገር ጋር በተያያዘ ለ19 ወራት ከእግር ኳስ ታግዶ ከቆየ በኋላ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በሞናኮ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡

ፈረንሳዊው አማካይ ፖል ፖግባ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ለሞናኮ 6 ጨዋታዎችን ብቻ ነው ያደረገው፡፡

የ33 ዓመቱ ተጫዋች በጉዳት ምክንያት ለሞናኮ የሚጠበቀውን ያህል ግልጋሎት መስጠት አልቻለም፡፡

ፖግባ ከቀናት በፊት ልምምድ ላይ አዲስ ጉዳት ማስተናገዱን ተከትሎ ክለቡ ውሉን ለማቋረጥ ጠይቆ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ሞናኮ ፖግባ በቀጣይ የእግር ኳስ ሕይወቱ መልካም ነገር እንዲገጥመው በመመኘት ከተጫዋቹ ጋር ተለያይቷል፡፡

የማንቼስተር ዩናይትድ እና የጁቬንቱስ የቀድሞ ኮከብ ከሀገሩ ፈረንሳይ ጋር በ2018 የዓለም ዋንጫን ማሳካቱ ይታወሳል፡፡

የፈረንሳዊው ኮከብ ፖል ፖግባ ቀጣይ ማረፊያ የሚጠበቅ ይሆናል፡፡