አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው በቀረቡ ምክረ ሀሳቦች ላይ የተጠናቀረው የመጨረሻ ሰነድ በነገው ዕለት ለሁሉም ቡድኖች ይቀርባል አለ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፡፡
የሀገራዊ ምክክር ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሒሩት ገ/ሥላሴ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤውን አሁናዊ ሁኔታ አስመልክተው በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ከስምንቱም ቡድኖች የቀረበውን ምክረ ሀሳብ ለማጣጣም የተቋቋመው ቡድን ምክረ ሀሳቦቹን አጣጥሞ ያደራጀው ሰነድ ለእያንዳንዱ ቡድን ቀርቦ ግብዓት እየተሰበሰበ ይገኛል፡፡
ይህ ሂደት በዛሬው ዕለት እንደሚጠናቀቅ የገለጹት ኮሚሽነሯ፥ የመጨረሻው ሰነድ ነገ ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ለሁሉም ተመካካሪዎች በጋራ እንደሚቀርብ ጠቁመዋል፡፡
ይህ ሂደት ምክክሩ ትልቅ ምዕራፍ ላይ መድረሱን ያመላክታል ነው ያሉት፡፡