የሀገር ውስጥ ዜና

ሞሀመድ አሊ ዩሱፍ ከአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ጋር ተወያዩ

By Mikias Ayele

August 21, 2026

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሞሃመድ አሊ ዩሱፍ ከናይጄሪያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት እና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልክተኛ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ  ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ሁለቱ ወገኖች በቀጣናዊ እና አህጉራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ማድረጋቸውን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በዚህ ወቅት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሞሃመድ አሊ ዩሱፍ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ በቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት እንዲሰፍን የሚያደርጉትን ጥረት አድንቀዋል፡፡