👉 ሀገራዊ ምክክሩ በሀገራችን የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ነው፡፡ 👉 በሀገራችን የነበሩትን ታሪካዊ ስብራቶች እንዲሁም የሐሳብ ልዩነቶች በጠብመንጃ እና በኃይል ሳይሆን በሰለጠነ መንገድ በምክክር ለመፍታት የሚያስችል አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ተከፍቷል፡፡ 👉 ሀገራዊ ምክክር ጉባኤው አሳታፊና አካታች በሆነ መልኩ ተካሂዷል፡፡ 👉 ማንኛውም የህብረተስብ ክፍል ሳይገለል፤ የሁሉም ድምጽ እንዲሰማና እዲከበር በትኩረት ተሰርቷል፡፡ 👉 በዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ላይ ከአራቱም የሀገራችን ማዕዘናት 4 ሺህ ተመካካሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ 👉 በሀገራዊ ምክክር ጉባኤው ለሀገራችን ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት የሚያስችሉ በስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ሰፊና ጥልቅ ምክከሮች ተካሂደዋል፡፡ 👉 አጀንዳዎቹ የሀገራችንን መሰረታዊ ችግሮች የዳሰሱና ለነገዋ ኢትዮጵያ መሰረት የሚጥሉ ናቸው፡፡ 👉 በመደማመጥና በመከባበር ለሀገራችን የተሻለ መፍትሄ በጋራ መፈለግ መቻላችን፤ ኢትዮጵያን አሁን ካለችበት ፈተና አውጥተው ወደተሻለ እና አዲስ ምዕራፍ የሚሻግሩ ናቸው፡፡ 👉 ይህ የጀመርነው የመደማማጥ ባህል ደምቆ ለትውልድ እንዲሻገር፤ ዘላቂ እሴታችን ይሆን ዘንድ የሁላችንም ቁርጠኝነት ያሰፈልጋል፡፡ በትዕግስት ግዛቸው