👉 ምክክሩ ፖለቲካዊ ተቃርኖ በይቅርታና በምክክር ጎዳና እንዲተካ መሰረት ጥሏል፡፡ 👉 ውጤቱ ለአሁኑ ብቻ ሳይሆን ለመጪው ትውልድ የሚተላለፍ አሻራ ነው፡፡ 👉 የሀገር ብርታት ያለው ልዩነትን በሰለጠነ መንገድ በውይይት መፍታት ላይ ነው፡፡ 👉 የዛሬዋ እለት ድምቀቷ እና ቁም ነገሯ ለሀገር የሚበጅ ለትውልድ የሚዋጅ አንድነታችንን የሚያጸና መልካም ተስፋችንን የሚያለመልም ሁኔታን የሰማንባት መሆንዋ ነው፡፡ 👉 የ130 ሚሊየን ህዝብን ሀሳብ ተሸክሞ ኃላፊነት ውሰድ ቀላል አይደለም፡፡ 👉 ተመካካሪዎች የነገን የህብር አንድነት እንድናይ፣ የሀሳብ የበላይነት እንዲሰፍን ማድረጋችሁ ታሪካዊ ስኬት ነው፡፡ 👉 በምክክሩ ለነገው ትውልድ የሚሻገር አሻራ ተቀምጧል፡፡ 👉 በሀገራዊ ምክክር የቀረቡ ሃሳቦች ለፖለቲካዊ ልምምዳችን እና ለሀገር ግንባታ ያላቸው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡ 👉 ምክክሩ የሁላችንም የሆነችውን ኢትዮጵያ የሚገልጹና የሚያጹኑ የጋራ ርዕይ እና እጣ ፈንታ በአንድ ላይ ለማስኬድ የሚያስችል እውቀት የተጨበጠበት ነው፡፡ 👉 የምክክሩ ማህበራዊ ፋይዳ በመከባበር እና በሰመረ ቋንቋ ከኃለ ቃል በጸዳ መልኩ ለመወያየት የሚያስችል አቅም እንዳለን አሳይቷል፡፡ 👉 በማህበራዊ አውዳችን ውስጥ መልክ መያዝ የሚኖርባቸዉ የፖለቲካ ቃላት እና ስንኞች ሰከን ያሉ እንዲሆኑ ተጨባጭ ልምድ ሰጥቷል፡፡ በእመቤት ሲሳይ