የሀገር ውስጥ ዜና

ሀገራዊ ምክክሩ የኢትዮጵያን ታላቅነት ዳግም ያሳየ ደማቅ ድል ነው – አቶ መሀመድ እድሪስ

By emebet sisay

August 22, 2026

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ የኢትዮጵያን ታላቅነት ዳግም ያሳየ ደማቅ ድል ነው አሉ የሰላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ፡፡

የሰላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ ለዘመናት የቆዩ መሠረታዊ ሀገራዊ ችግሮችን በሠለጠነ መንገድ በውይይት እና በምክክር ለመፍታት የተጀመረው ታሪካዊው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ በስኬት መጠናቀቁን አስመልክተው ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ይህ ታሪካዊ ሂደት በሰላም፣ በታማኝነት፣ በታላቅ የኃላፊነት ስሜት እና በኢትዮጵያዊ ጨዋነት መጠናቀቁን አድንቀዋል።

ሀገርን ለማሻገር በብልሃት መክሮ፣ ትውልድን አስተሳስሮ ሌላ ዓድዋ ሰርቶ ማለፍ መታደል መሆኑን ጠቁመውነው፤ ተከብሮ የመኖርን መሰረትም ያጸናል ነው ያሉት፡፡

ሀገራችን የመከረችበት ይህ ጉባኤ የሕዝብን አሸናፊነት፣ የኢትዮጵያን ታላቅነት፣ የራስን ችግር በራስ የመፍታት ጥበብን እና የዓላማ አንድነትን በገሃድ ለዓለም ዳግም ያሳየ ነው ብለዋል፡፡

በምክክሩ የተገኙ የጋራ መግባባቶችን እና የሰላም ፍሬዎችን መንከባከብ እና መጠበቅ የሁሉም ዜጋ የጋራ ኃላፊነት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

መላው ኢትዮጵያውያን ተባብረው የነገዋን ጠንካራ፣ የበለጸገች እና ሁለንተናዊ ሰላሟ የተጠበቀ ኢትዮጵያን መሰረት እንዲያጸኑ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።